ሰሞኑ አዲስ መረጃ / information

ስፖርት/Sport

  

   የምግብ አዘገጃጀት/Recip

                      
አዘገጃጀቱ፡- በመጀመሪያ ድንቹን ልጦ ለሁለት መከተፍ፡ ቀጥሎ በመጥበሻ ላይ ዘይቱን ጨምሮ  አግሎ የተከተፈውን ድንች ጨምሮ መጥበስ: ከተጠበሰ በኋላ ሲበስል ዘይቱን እንዲመጥ  
በወረቀት ላይ ማስቀመጥ፡ ቀጥሎ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩት እና ጅንጅብል በደቃቁ ከትፎ አንድ ላይ መጨመር ቀጥሎ ቲማቲም በደቃቅ ከትፎ ከሽንኩርት ጋር አብሮ ማብሰል፤ ሦስት አጥንቱ የወጣ የዶሮ ሥጋ ሦስት ቦታ ከትፎ ከሽንኩርቱ ጋር አብሮ ማብሰል ለትንሽ ደቂቃ መጥበሻውን ከድኖ መጠበቅ፤ በመቀጠልም ሩብ ኪሎ የሚሆን በስመቲ ሩዝ መቀቀል፤እሱ እስኪበስል አንድ ራስ ቀይ ሽንኩርት፣ ነጭ ሽንኩርት እና ጅንጅብል በደቃቁ ከትፎ ማብሰል እሱ ላይ ቁንዶ በርበሬ፣ ቀረፋ እና ቁሩንፍድ ጨምሮ አብሮ ማብሰል ቀጥሎ የተቀቀለውን ሩዝ የዶሮ ስጋ እና ከተጠበሰው ድንች ጋር አብሮ እንድ ለ 30 ደቂቃ እብስሎ፡፡ ከበሰለ በኋላ የፐርስሊ ቅጠል በደቃቁ ክትፎ መነስነስ ከዛስ መመገብ፡፡

              መልካም በዓል ይሁንላችሁ!!!!!!!!!!!!!!!

 ዘወትር ከመላው ዓለም ያሰባሰብናቸው የፎቶ መረጃዎችን ለእናተ ይመጥናሉ ያልናቸውን  እናቀርባለን፡፡ ተመሣሣይ መረጃ ካሎት This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. This email address is being protected from spambots. You need JavaScript enabled to view it. እና ፌስ ቡክ ገጻችን ላይ infonegari ይላኩልን፡፡    

 

                                        የዛሬ  የዝውውር ዜናዎች

 

፡-  ሪያል ማድሪድ ሄምስ ሮደሪጌዝን ከሞናኮ በ£71ሚ አስፈርሞታል፡፡ ማድሪድ በ2014 የዓለም ዋንጫ  ድንቅ እንቅስቃሴ ያሳዩትን ቶኒ ክሮስን እና ሮድሪጌዝን ማስፈረሙ ተከትሎ አንዳንድ ተጫዋቾች ክለቡን ይለቃሉ ተብሎ የጠበቃል፡፡ እነዚህም ተጫዋቾች ዲማሪያ፣ሳሚ ከዲር እና ኢስኮ ናቸው፡፡

 

፡- የዓለማችን ድንቅ ተጫዋች ሜሲ ከአንድ ዓመት በፊት ወደ አርሴናል መግባት ፈልጎ እንደ ነበር  ዘገበ፡፡ ሜሲ አያይዞም በአርሰን ዌንገር መሰልጠን ምኞቱ እንደሆነም ተኛግሯል፡፡

 

፡- አርሴናል ኮሎምቢዊውን ግብ ጠባቂ ዴቪድ ኦስፒናን በ£3ሚ  ለማስፈረም ከጫፍ ደርሷል፡፡

 

፡- ባርሴሎና የቫሌንሽያውን ተከላካይ ጀርመናዊው ጀርሚ ማቲውን  በ£15.8ሚ አስፈረመ ፡፡

 

፡- አጥቂ ከዚህ ከሳንቼዝ በኋላ አናስፈርም ያሉት የአርሴናሉ አሰልጣኝ አርሴን ዌንገር ፤ ዛሬ እነደወጣው  መረጃ ከሆነ አርሴናሎች ተጨማሪ አጥቂ ሊያስፈርሙ ከፖርቶ ጋር እየተነጋገሩ እነደሆነ ነው፡፡ ሊያስፈርሙት የፈለጉት ተጫዋች  ኮሎማቢያዊው ጃክስን ማርትሬዝ ነው፡፡

 

ጥበብ/Art

“የጠፋው ቤተሰብ” ለንባብ በቃ
በየሺወርቅ ወልዴ የተፃፈው እና በእውነተኛ ታሪክ ላይ የተመሰረተው “የጠፋው ቤተሰብ” የተሰኘ ልብ ወለድ መፅሐፍ ለንባብ በቃ፡፡ መፅሀፉ በውስጡ ሌሎች አጫጭር ታሪኮችና ግጥሞች የተካተቱበት ሲሆን ለደራሲዋ ሁለተኛ ስራዋ እንደሆነም ታውቋል፡፡ “የጠፋው ቤተሰብና ሌሎችም” መፅሐፍ 122 ገፆች ያሉት ሲሆን ደራሲዋ ከዚህ ቀደም “አትሮኖስ” የተሰኘ የግጥም መፅሀፍ ለንባብ አብቅታለች፡፡ በሌላ በኩል በገጣሚ ውድነህ ግርማ (የአስቴር ልጅ) የተፃፈው “ሽበቴን ለቅማችሁ” የተሰኘ የግጥም መድበል ሰሞኑን በገበያ ላይ ውሏል፡፡ ከ120 በላይ አጫጭር ግጥሞችን የያዘው መጽሐፉ፤በ65 ገፆች የተቀነበበ ሲሆን ግጥሞቹ በፍቅር፣ በማህበራዊ ኑሮ፣ በታሪክና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ ያጠነጥናሉ፡፡ ወጣቱ ገጣሚ የግጥም መድበሉ የበኩር ስራው እንደሆነ ጠቅሶ ወደፊት ሊያሳትም ያዘጋጃቸው የልብወለድ ስራዎች እንዳሉትም ገልጿል፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ 31 March, 2014
“ስንክርተነ” የተባለ የጉራጊኛ የግጥም መፅሀፍ
የቤተ ጉራጌ ባህል ማዕከል ዋና ስራ አስኪያጅ በሆኑት በአቶ ተስፋዬ ጐይቴ የተፃፈው “ስንክርተነ” 135 ግጥሞችን ያካተተውና በ140 ገፆች ላይ የተመጠነው መፅሀፉ፤ በጉራጊኛ ቋንቋ የተዘጋጀ ሲሆን አብዛኞቹ ግጥሞች የጉራጌን ባህል፣ ወግና ትውፊት ያስቃኛሉ ተብሏል፡፡ ትልቁን የነፃነት ታጋይ የኔልሰን ማንዴላን ህይወት የተመለከተ ረጅም ግጥም እንደተካተተበትም አቶተስፋዬጐይቴገልፀዋል፡፡ በሴትኛ አዳሪነት ህይወት እና በሌሎችም ማህበራዊ ህይወት ላይ ትኩረት ያደረገ ሲሆን ፀሀፊው ከዚህ በፊት “የኬርጋት” እና “ጉራጌንዶ” የተሰኙ የግጥም መፃህፍትን በጉራጊኛ ቋንቋ ፅፈው ለንባብ አብቅተዋል። ሶስተኛውና “ስንክርተነ” የተሰኘው የግጥም መፅሀፍ በጃፋር መፅሀፍ መደብር እየተከፋፈለ ነው፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ
“የንጉሱ ገመና”
በጋዜጠኛ ግርማ ለማ የተፃፈውና በቀዳማዊ ሀ/ስላሴ የቤት ውስጥ ውሎ፣ ቤተሰባዊ ህይወትና የጓዳ ታሪክ ላይ የሚያጠነጥነው “የንጉሱ ገመና” ለንባብ በቅቷል፡፡ መፅሀፉ እስከ ዛሬ በንጉሱ ዙሪያ ከተፃፉት መፅሀፎች የሚለየው በቤት ውስጥ ውሏቸውና ገመናቸው ላይ የሚያተኩር በመሆኑ ነው ተብሏል፡፡ 170 ገፆች ያሉት መፅሀፉ፤ በአርጋኖ የህትመት ኢንዱስትሪ ታትሞ በጃፋር መፅሀፍ መደብር እየተከፋፈለ ነው፡፡
ምንጭ አዲስ አድማስ

Bookmark and Share

Support

Contact us

Teliyodan Information & Promotion Service
MAIN OFFICE KOLFE KERANYO WOREDA 09 INFRONT OF ZELALEM BLDG.
MILLEFOGLLE SITE CONDOMINIUM
GROUND FLOOR
Tele 0113 714382
Mob. 0911 20 94 87
EMAIL: info@infonegari.com

Subscribe for Tender/Auction Alert